Adwa Victory – 100th Anniversary – Speech at UCLA

ADWA’s 100th Anniversary event at UCLA from TSEHAI Films on Vimeo.

 

The March 1996 event at UCLA was organized by the United Young Ethiopians in Los Angeles and other community organizations to commemorate Adwa’s Centenary Celebration.

 

አድዋ [አባቶቻችን] ጀግንነታቸውን ለዓለም ሕዝብ ያሳዩበት፣ ለአፍሪካ ወንድሞቻችን መኩሪያና ምሳሌ የሆንበት፣ አውሮፓንና ቀሪውን ወራሪ ኃይል ያስደነገጥንበት፤ በተለይ የጣሊያንን ወራሪ መንግስት በዓለም ፊት ያዋረድንበት ታላቅ በዓል ነው። ዛሬ በሰው ሀገር በዘርና በክልል (ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምሥራቅና ምዕራብ) ብለን ሳንከፋፈል ሁላችንም በኢትዮጵያዊነታችን የአያቶቻችንን ገድል ልንዘክር በጋራ መገኘታችን ለታሪካችንና ለማንነታችን ያለንን ታላቅ አክብሮት ያሳያል። እንደልዩነታችን ሁሉ የተላበስነው ታሪካዊ ውበትና ግርማ በጋራ በኢትዮጵያዊነታችን ተንጸባርቆ ያለንን አንድነትም ይመሰክራል።

ይህን በዓል ልዩ የሚያደርገው በሰው ሀገር መቶኛ ኣመቱን ማክበራችንና በሀገራችን መሪዎች አዲስ ታሪክ መዘጋጀቱ ብቻ ሳይሆን እኛ ወጣቶች በህብረት አባቶቻችንና ታላላቅ ወንድሞቻችንን በተለይ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን በጋራ አሰባስበን ለወደፊት ሊያደርጉ የሚገባቸውን የጋራ ጉዞ ፈር በመቅደዳችን ነው።

የአድዋን መቶኛ ዓመት [የድል] በዓል በምናከብርበት [በአሁኑ] ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአውሮፓ በመጣው ጣልያን ሳይሆን ማንነታቸውን በካዱ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን የአመራር ቀንበር ስር ወድቆ መብቱ ሲጣስ፣ ድንበሩ ሲቆረስና ሲወረስ፣ ማንነቱ ሲሸጥና ሲለውጥ፣ ታሪኩንም ሲካድና በአዲስ ሲለወጥ፣ ለሚመለከተው ለእኛው ትውልድ ታላቅ የታሪክ ኃላፊነት አለብን።

ይህን ሳንወድ በግዳችን በጊዜያችን የተፈጠረውን የትውልድ አደራ ለመወጣት ሁላችንም በአንድነት የበኩላችንን ኃላፊነት ከተወጣን  ዛሬ ልናከብር የተሰበሰብነውን ድል የሚያክል ለትውልድ ሊተላለፍ የሚችል መዘክር ልናስተላልፍ እንችላለን። ያለበለዚያ ግን እየወረድን ባለንበት የታሪክ አዘቅጥ ውስጥ ተወዝፈን ለዓለም ሕዝብ መሳለቂያ እና ለሚቀጥለውም ትውልድ መተዛዘቢያ እንደምንሆን አልጠራጠርም።

በዚህ ታሪካችን፣ ባሕላችንና በአጠቃላይ ማንነታችን አጠያያቂ ሁኔታ ላይ በወደቀበት ታሪካዊ ወቅት በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሳይሆን፣ አምባሳደሮች መባል አለብን። እያንዳንዳችን ያለብንን ኃላፊነት ከተወጣን ባህላችንን እና ታሪካችንን ከጠበቅን፣ ጥቂት የመንግስት ባለስልጣናት የሚያደርጉትን ታሪክን የማጥፋት ዘመቻ ማቆም እንችላለለን። ነገር ግን እስካሁን ስናደርግ እንደቆየነው ሌላውን ጠብቀን መኖር ካሻን በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ታሪክ የለሽ ትውልድ ሆነን የታሪካችንን ምንጭ ፍለጋ ተክል በሌለበት በረሃ ላይ ስር ፍለጋ ቁፋሮ እንጀምራለን።

ታሪካዊ ማንነታችንን ለማስታወስና ለማደስ በተሰበስብንበት በአሁኑ ወቅት ያልተበረዘና ያልተከለሰ ንጹህ ታሪካዊ ባህላችንን ማየትና መስማት እንድንችል ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ላሉ የሥነጥበብና የኪነጥበብ ባለሞያዎች በመላው ኢትዮጵያዊ ወጣቶች እና ዛሬ ይህን በዓል በጋራ ለማክበር በተሰበሰብነው ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ላቀርብ እፈልጋለሁ። . . . ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም፣ አንድነት እና ብልጽግና ምኞታችን ብቻ ሳይሆን ጥረታችንም ይሁን።

Share this post

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest
Share on print
Share on email

Recent News

“ኢትዮጵያን ገፍተን ገፍተን ገደሉ ጫፍ እያደረስናት ነው “ኤልያስ ወንድሙ የፀሐይ አሳታሚ መስራችና ስራ አስኪያጅ -ክፍል 2 – ARTS WEG

“ኢትዮጵያን ገፍተን ገፍተን ገደሉ ጫፍ እያደረስናት ነው::” ኤልያስ ወንድሙ የፀሐይ አሳታሚ መስራችና ሥራ አስኪያጅ @Arts Tv World​. ስለወቅታዊ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታዎች ከአርትስ ቲቪ ኃላፊ ከአዜብ ወርቁ