የአዲስ አበባ ከተማ ቤተ መፃህፍት ግንባታ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ተጣለ

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ጥቅምት 4/2012 ዓ.ም.)

የአዲስ አበባ ከተማ ቤተ መፃህፍት ግንባታ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ በአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተቀምጧል፡፡ የቤተ መፃህፍቱን ፕሮጀክት ግንባታ የሚያካሄደው ቫርኔሮ የተባለ የጣሊያን ስራ ተቋራጭ ኩባንያ ሲሆን የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ሚስተር ቫርኔሮ የመሰረት ድንጋይ ስነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ይህን እድል በማግኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ ግንባታውን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ሰርተን እናስረክባለን ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በበኩላቸው በመሃል ከተማ የእውቀት ማዕከል መገንባቱ ለሃገሪቱ ዜጎች ትልቅ ስጦታ መሆኑን በመግለፅ ለታላቁ ቤተ መፃህፍት የሚመጥን ስም እንዲያወጡ ለከተማዋ ነዋሪዎች ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የፀሐይ አሳታሚ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ኤልያስ ወንድሙ የዲጂታል ቤተ መጻህፍቱ ለሃገሪቱ ታሪካዊ እና ነባር ቅርስ የሆኑ ጽሁፎችን ለትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል፡፡ በአንድ ጊዜ ከ10 ሺህ ሰው በላይ ማስተናገድ የሚችለውን የዘመናዊ ቤተ መፃህፍቱን ግንባታ ፕሮጀክት ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በይፋ አስጀምረዋል፡፡ በ38 ሺህ 687 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈውና ከአራት ኪሎ ፓርላማ ፊት ለፊት ካለው አርበኞች ህንፃ አጠገብ የሚገነባው ፕሮጀክቱ ከ130 በላይ መኪኖችን ማቆም የሚችል የመኪና ማቆሚያ ቦታም ይኖረዋል፡፡

Share this post

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest
Share on print
Share on email

Recent News

“ኢትዮጵያን ገፍተን ገፍተን ገደሉ ጫፍ እያደረስናት ነው “ኤልያስ ወንድሙ የፀሐይ አሳታሚ መስራችና ስራ አስኪያጅ -ክፍል 2 – ARTS WEG

“ኢትዮጵያን ገፍተን ገፍተን ገደሉ ጫፍ እያደረስናት ነው::” ኤልያስ ወንድሙ የፀሐይ አሳታሚ መስራችና ሥራ አስኪያጅ @Arts Tv World​. ስለወቅታዊ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታዎች ከአርትስ ቲቪ ኃላፊ ከአዜብ ወርቁ